ልደት እና ቅዱስ መነሻ
የቀኝ ጌታ አባ መዝሙር ሐዋዝ የዜማ ቃላት እና ታሪካዊ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ከነበሩት ከአባታቸው ሊቀ ማዕምራን ሐዋዝ ጥሩነህ እና ከእናታቸው እማሆይ አጠናሽ ተበጀ ታህሳስ 19/1912 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ግምጃ ቤት ማርያም ቤተክርስቲያን ግቢ ተወለዱ።
In Loving Memory · መታሰቢያ
በእምነት፣ በፍትህ እና በቤተሰብ ቅርስ የተሞላ ምዕተ ዓመት

የአባታችን ቡራኬ
"እንዴት ሰንብታችኋል? ደህና አርፋችኋል? ቤታችሁ ውስጥ ሁሉም ሰላም ነው? እኔ ደግሞ ደህና ነኝ፣ እግዚአብሔር ይመስገን። እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይጠብቅ። ጌታ መድኃኒዓለም ይባርካችሁ፣ ይምራችሁ፣ ረጅም ዕድሜ ይስጣችሁ። አሜን። እግዚአብሔር ሲፈቅድ እንገናኝ።"
The Extraordinary Life
የቀኝ ጌታ አባ መዝሙር ሐዋዝ የዜማ ቃላት እና ታሪካዊ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ከነበሩት ከአባታቸው ሊቀ ማዕምራን ሐዋዝ ጥሩነህ እና ከእናታቸው እማሆይ አጠናሽ ተበጀ ታህሳስ 19/1912 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ግምጃ ቤት ማርያም ቤተክርስቲያን ግቢ ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ከፊደላት እስከ መዝሙረ ዳዊት ድረስ በግምጃ ቤት ማርያም ተምረዋል። ከመምህር ዜናዊ ውዳሴ ማርያምን፣ አንቀጸ ብርሃን፣ መልክአ ማርያምና መልክአ ኢየሱስን ተምረዋል። ከመምህር ገብረኢየሱስ አቋቋም ተምረው በአቡነ ሚካኤል ሲመተ ዲቁና ተቀብለዋል። ከመምህር ገብረሥላሴ ቅኔ ተምረው የቀኝ ጌታነት ማዕረግን አግኝተዋል።
በ1950 ዓ.ም ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጠና የወሰዱ ሲሆን በጎንደር ከተማ የአጥቢያ ዳኛ ሆነው ሰርተዋል። በጠበቃነት ከ30 ዓመታት በላይ አገልግለዋል። በጎንደር ከተማም የጠበቆች ማህበር አባል ነበሩ።
ከእማሆይ እመቤት አስካለ ጋር ቅዱስ ጋብቻ መስርተው ሲኖሩ ከቆዩ በኋላ ህዳር 21/2003 ዓ.ም በወቅቱ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሥርዓተ ቡራኬና ምንኩስና ተፈጽሞላቸዋል። ሳይታወኩ አርጅተው ቀሪ ዘመናቸውን በፀሎት፣ በፆም እና በምስጋና ያሳልፉ ታላቅ አባት ነበሩ።
የሚያርፉበትን ቀን አውቀው ግንቦት 7 ቀን መቼ ነው ብለው ጠይቀው፣ በተወለዱ በ106 ዓመታቸው ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ያለምንም ስቃይና ህመም ማለዳ በረድኤት ቆይተው ወደ ጌታቸው አርፈዋል።
1912 — 2018
1912 ዓ.ም
ታህሳስ 19 በግምጃ ቤት ማርያም ቤተክርስቲያን ግቢ።
Early Years
ከሦስት መምህራን ተምረው፤ በአቡነ ሚካኤል ዲቁና ተቀብለዋል።
—
ቅኔን ተምረው የቀኝ ጌታነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።
1950 ዓ.ም
በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሥልጠና ወስደው ከ30 ዓመታት በላይ አገልግለዋል።
2003 ዓ.ም
ህዳር 21 ከእማሆይ እመቤት አስካለ ጋር በአቡነ ኤልሳዕ ሥርዓተ ምንኩስና ተፈጽሟል።
2018 ዓ.ም
ግንቦት 7 በ106 ዓመታቸው ያለ ስቃይ አርፈዋል።

የዘላለም ቅርንጫፍ
ልጆቻቸውን በሙሉ አስተምረው፣ አሳድገው፣ አጋብተው ለወግ ማዕረግ ያበቁ የተወደደ አባት፣ አያትና ቅድመ-አያት ነበሩ።
የቤተክርስቲያን መታሰቢያ
የመህለት ጥልቅ ምስጋናዎች አባ መዝሙር ሲጠብቁት የኖሩትን ትውፊት ያሰማሉ።
"ማርያም… እመ አምላክ… ንባርክኪ…"
የሚንቀሳቀሱ ትዝታዎች
የተጠበቁ አጭር ቅጽበቶች — ድምፃቸው፣ ቡራኬያቸው፣ ጸጥ ያለ ግርማቸው።
የአባታችን የቀኝ ጌታ አባ መዝሙር ሐዋዝን ነፍስ ፈጣሪ በቀኙ ያድርግልን ዘንድ እንመኛለን። አሜን።
— በፍቅር፣ ቤተሰቦቻቸው